← ወደ ብሎግ
July 3, 2026

ትክክለኛው የማጠናቀቂያ ስራ ቅደም ተከተል — ዘመናዊ አሰራር

ከፍተኛ ጥራት ላለው የቤት ማጠናቀቂያ ፕሮጀክት፣ አንድ ስራ ሌላውን እንዳይጎዳ ትክክለኛ ቅደም ተከተል መከተል አለበት። በሱፍቃድ የምንከተለው ዘመናዊ 16-ደረጃ ቅደም ተከተል ይኸው።

ትክክለኛው የማጠናቀቂያ ስራ ቅደም ተከተል — ዘመናዊ አሰራር
  1. 1. ግድግዳውን ይመርምሩ እና የግድግዳ ማስተካከያ ያድርጉ

    • •ስንጥቅ (ክራክ) ካለ ይድፈኑ።
    • •ያልተስተካከሉ ግድግዳዎችን እና ጠርዞችን ያስተካክሉ።
    • •መላውን ሕንፃ ያጽዱ።
  2. 2. የቧንቧ ስራ

    • •የውሃ አቅርቦት ቧንቧዎችን ይስሩ።
    • •የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎችን ይስሩ።
    • •የመጸዳጃ ቤት እና የመታጠቢያ ቤት የቧንቧ ስራዎችን ይስሩ።
    • •ግድግዳዎቹን ከመዝጋትዎ በፊት ሁሉንም የውሃ መስመሮች ሙከራ ያድርጉ።
  3. 3. ኤሌክትሪክ (የመጀመሪያ ስራ)

    • •ኮንዲት፣ እስካቶላ እና የብሬከር ቦክስ ይስሩ።
    • •ተገቢ በሚሆንበት ጊዜ ሽቦውን ይጎትቱ።
    • •ኢንተርኔት፣ ቴሌቪዥን እና የደህንነት ካሜራ መስመሮችን ይስሩ።
  4. 4. የጂብሰም ቦርድ ስራ

    • •በቻይና ወይም በሀገር ውስጥ ቦርድ ይስሩ።
    • •የመብራት ቦታዎችን ያዘጋጁ።
  5. 5. የግድግዳ ቻክ / ፑቲ

    • •ቻክ ለውስጣዊ ግድግዳዎች።
    • •ፑቲ ለውጫዊ ግድግዳዎች።
    • •በአግባቡ እስከሚደርቅ ይታገሱ።
  6. 6. መሬቱን ፈረካስ ማድረግ

    • •ሙሉ በሙሉ እንዲደርቅ ያድርጉ።
  7. 7. ወተር ፕሩፍ

    • •መታጠቢያ ቤቶች።
    • •መጸዳጃ ቤቶች።
    • •በረንዳዎች።
    • •ኩሽናዎች (አስፈላጊ ከሆነ)።
    • •የውሃ ማጠራቀሚያዎች።
  8. 8. የሴራሚክ ስራ

    • •የመታጠቢያ ቤት ግድግዳዎች።
    • •የወጥ ቤት ግድግዳዎች።
    • •የውጪ ግድግዳ እንደ አስፈላጊነቱ።
  9. 9. የወለል ንጣፎች / የሴራሚክ ስራ

    • •ሳሎን።
    • •መኝታ ቤቶች።
    • •ወጥ ቤት።
    • •መታጠቢያ ቤቶች።
    • •ኮሪደሮች።
  10. 10. መቀባት

    • •ፕራይመር።
    • •የመጀመሪያ ዙር።
    • •ሁለተኛ ዙር።
    • •የመጨረሻ የማጠናቀቂያ ቀለም።
  11. 11. በሮች እና መስኮቶች መግጠም

    • •በሮች መግጠም።
    • •መቆለፊያዎችን መግጠም።
    • •መስኮቶችን መግጠም።
    • •መስታወት መግጠም።
  12. 12. ኤሌክትሪክ (ሁለተኛ ዙር)

    • •ማብሪያና ማጥፊያዎች።
    • •ሶኬቶች።
    • •ብሬከር።
    • •አንፐሎች።
  13. 13. የቧንቧ ስራ ሁለተኛ ዙር

    • •መጸዳጃ ቤቶች።
    • •የመታጠቢያ ገንዳዎች።
    • •የሻወር መፈሳሻ።
    • •የወጥ ቤት ማጠቢያ።
    • •የውሃ ማሞቂያ ገጠማ።
  14. 14. የኪችን ካቢኔቶች እና ቁምሳጥን ገጠማ

    • •ካቢኔቶችን መግጠም።
    • •የልብስ ማስቀመጫዎችን ቁምሳጥን ገጠማ።
  15. 15. የመጨረሻ ጽዳት

    • •የተንጠባጠበ ቀለም ካለ መሬቱን ያፀዱ።
    • •በርና መስኮቶችንም ያፀዱ።
  16. 16. የመጨረሻ ሁሉንም መሞከር

    • •ኤሌክትሪክን ይፈትሹ።
    • •የቧንቧ መስመሮችን ይፈትሹ።
    • •ቀለም ይፈትሹ።
    • •በሮች እና መስኮቶችን ይፈትሹ።
    • •ከማስረከብዎ በፊት ጉድለቶችን ያስተካክሉ።

ይህ ቅደም ተከተል እንደገና ስራዎችን እንዳትሰሩ ያግዛል። በሱፍቃድ የፊኒሺንግ ስራ ነው — ቅንጡ ህይወት ይገባዎታል።

በTelegram ይገኙንTelegram

በTelegram ይገኙን

“ትክክለኛው የማጠናቀቂያ ስራ ቅደም ተከተል — ዘመናዊ አሰራር” — በTelegram ጠይቁን፣ በ24 ሰዓት ውስጥ መልስ ይደርስዎታል።

@besu0060968 346 363 · አዲስ አበባ