← ወደ ብሎግ
July 3, 2026
ትክክለኛው የማጠናቀቂያ ስራ ቅደም ተከተል — ዘመናዊ አሰራር
ከፍተኛ ጥራት ላለው የቤት ማጠናቀቂያ ፕሮጀክት፣ አንድ ስራ ሌላውን እንዳይጎዳ ትክክለኛ ቅደም ተከተል መከተል አለበት። በሱፍቃድ የምንከተለው ዘመናዊ 16-ደረጃ ቅደም ተከተል ይኸው።

1. ግድግዳውን ይመርምሩ እና የግድግዳ ማስተካከያ ያድርጉ
- •ስንጥቅ (ክራክ) ካለ ይድፈኑ።
- •ያልተስተካከሉ ግድግዳዎችን እና ጠርዞችን ያስተካክሉ።
- •መላውን ሕንፃ ያጽዱ።
2. የቧንቧ ስራ
- •የውሃ አቅርቦት ቧንቧዎችን ይስሩ።
- •የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎችን ይስሩ።
- •የመጸዳጃ ቤት እና የመታጠቢያ ቤት የቧንቧ ስራዎችን ይስሩ።
- •ግድግዳዎቹን ከመዝጋትዎ በፊት ሁሉንም የውሃ መስመሮች ሙከራ ያድርጉ።
3. ኤሌክትሪክ (የመጀመሪያ ስራ)
- •ኮንዲት፣ እስካቶላ እና የብሬከር ቦክስ ይስሩ።
- •ተገቢ በሚሆንበት ጊዜ ሽቦውን ይጎትቱ።
- •ኢንተርኔት፣ ቴሌቪዥን እና የደህንነት ካሜራ መስመሮችን ይስሩ።
4. የጂብሰም ቦርድ ስራ
- •በቻይና ወይም በሀገር ውስጥ ቦርድ ይስሩ።
- •የመብራት ቦታዎችን ያዘጋጁ።
5. የግድግዳ ቻክ / ፑቲ
- •ቻክ ለውስጣዊ ግድግዳዎች።
- •ፑቲ ለውጫዊ ግድግዳዎች።
- •በአግባቡ እስከሚደርቅ ይታገሱ።
6. መሬቱን ፈረካስ ማድረግ
- •ሙሉ በሙሉ እንዲደርቅ ያድርጉ።
7. ወተር ፕሩፍ
- •መታጠቢያ ቤቶች።
- •መጸዳጃ ቤቶች።
- •በረንዳዎች።
- •ኩሽናዎች (አስፈላጊ ከሆነ)።
- •የውሃ ማጠራቀሚያዎች።
8. የሴራሚክ ስራ
- •የመታጠቢያ ቤት ግድግዳዎች።
- •የወጥ ቤት ግድግዳዎች።
- •የውጪ ግድግዳ እንደ አስፈላጊነቱ።
9. የወለል ንጣፎች / የሴራሚክ ስራ
- •ሳሎን።
- •መኝታ ቤቶች።
- •ወጥ ቤት።
- •መታጠቢያ ቤቶች።
- •ኮሪደሮች።
10. መቀባት
- •ፕራይመር።
- •የመጀመሪያ ዙር።
- •ሁለተኛ ዙር።
- •የመጨረሻ የማጠናቀቂያ ቀለም።
11. በሮች እና መስኮቶች መግጠም
- •በሮች መግጠም።
- •መቆለፊያዎችን መግጠም።
- •መስኮቶችን መግጠም።
- •መስታወት መግጠም።
12. ኤሌክትሪክ (ሁለተኛ ዙር)
- •ማብሪያና ማጥፊያዎች።
- •ሶኬቶች።
- •ብሬከር።
- •አንፐሎች።
13. የቧንቧ ስራ ሁለተኛ ዙር
- •መጸዳጃ ቤቶች።
- •የመታጠቢያ ገንዳዎች።
- •የሻወር መፈሳሻ።
- •የወጥ ቤት ማጠቢያ።
- •የውሃ ማሞቂያ ገጠማ።
14. የኪችን ካቢኔቶች እና ቁምሳጥን ገጠማ
- •ካቢኔቶችን መግጠም።
- •የልብስ ማስቀመጫዎችን ቁምሳጥን ገጠማ።
15. የመጨረሻ ጽዳት
- •የተንጠባጠበ ቀለም ካለ መሬቱን ያፀዱ።
- •በርና መስኮቶችንም ያፀዱ።
16. የመጨረሻ ሁሉንም መሞከር
- •ኤሌክትሪክን ይፈትሹ።
- •የቧንቧ መስመሮችን ይፈትሹ።
- •ቀለም ይፈትሹ።
- •በሮች እና መስኮቶችን ይፈትሹ።
- •ከማስረከብዎ በፊት ጉድለቶችን ያስተካክሉ።
ይህ ቅደም ተከተል እንደገና ስራዎችን እንዳትሰሩ ያግዛል። በሱፍቃድ የፊኒሺንግ ስራ ነው — ቅንጡ ህይወት ይገባዎታል።
TelegramበTelegram ይገኙን
“ትክክለኛው የማጠናቀቂያ ስራ ቅደም ተከተል — ዘመናዊ አሰራር” — በTelegram ጠይቁን፣ በ24 ሰዓት ውስጥ መልስ ይደርስዎታል።
@besu0060968 346 363 · አዲስ አበባ



